YOUNGERVERSION

just a free corner

let us talk about particular ppl…meaning…

dont generalize no more

May 3, 2009 Posted by meseret | mesi | | No Comments Yet

ሽሽት

shishitገና ከማለዳው ከህጻንነቴ ሸሸሁ:: ነፍስ ያወቀች አስተዋይ ልጅ ለመባል ተመኝቼ…፡፡

 ከታዳጊነት ግዜዬም ሸሽቻለሁ የቀን ህልሜ ወጣት መሆን መደሰት መቦረቅ መዝለል ነበርና፡፡

 ዛሬ ከወጣትነቴ እየሸሸሁ ነው፡በተራዬ የበሰለች አስተዋይ ሴት መሆን እፈልጋለሁ፡፡

 ነገስ? ነገ ደግሞ ከጎልማሳነቴ እሸሻለሁ፡፡የእድሜዬን ጭራ ለመያዝ እንደተንደረደርኩ ህይወትም በክፉ ስላቁዋ እንዳደነቆረችኝ ከጫፏ መድረሴ ነው፡፡

 ይኸው ነው፡፡ያላዋቂነት ወግ ማእረግ፡፡ነገን የመናፈቅ አባዜ፡፡ ዛሬን የመጥላት ጥውንት፡፡

May 3, 2009 Posted by meseret | mesi | | 1 Comment