እንባሽ
የልብሽ ስር የእንባ ምንጩ
መንጠፉን ልቤ ሲአውቀው
ስር የያዘ ጥላቻሽን
ቀልቤ ነግሮኝ ባይኔ አይቼው
ስ-ቅ-ስ-ቅ አልሽ አሉ በፍቅሬ
እውን እንባሽ እንባ ነው?
ወይስ ቃሉን መረጡልኝ
`እንባ` ልቤን እንዲየደማው
በቃል ፍቅርን መዝራት እንጂኮ
ጥላቻ ማብቀል ቀላል ነው…
ምነው እያየነው?
እንደዳር አገር ቀስት ጫፍ
ቃልምኮ መርዝ ይቀባል
ከደጋኑ ሲስፈነጠር
ወይ ይመታል ወይ ይስታል
እንባ ቃሉ ልብ ይወጋል
ቃሉም እንደቀስቱ ጫፍ
ልብ ያደማል ልብ ያቆስላል
እውቀትን ፍለጋ
ጌትነት እንየው
No comments yet.
Leave a comment
-
Archives
- November 2009 (2)
- June 2009 (1)
- May 2009 (2)
- March 2009 (2)
- February 2009 (6)
- January 2009 (3)
- July 2008 (2)
- June 2008 (5)
-
Categories
-
RSS
Entries RSS
Comments RSS
